እርም በሉ ብአዴን! እነሆ! [ክፍል ፩] አቻምየለህ ታምሩ

ብአዴን ከወልድያ ሕዝብ ጋር ያካሄደው ውይይት

የፋሽስት ወያኔው ነውረኛ ድርጅት ብአዴን የትግራይ ወታደሮች በወሎ ያካሄዱትን የጭካኔ ጭፍጨፋ ተከትሎ ከወልድያ ሕዝብ ጋር ያካሄደው «ውይይት» ያዳምጡት።

 

ነውረኛው ብአዴን የአማራን ሕዝብ ያወገዘበትን መግለጫ ያወጣው ይህንን የመሰለ የሕዝብ ለቅሶና ምሬት ከሰማና ካየ በኋላ ነው።

ብአዴን «ኢሰብአዊ ጥሰት ሊያደርስ በሚችል መንገድ እየተሰራ ያለ ስራ በሕግ አስከባሪው ዘንድ እንደሌለ መታወቅ አለበት» የሚል መግለጫ ያወጣው ግፉዓን ከታች በሚደመጠው መልክ «የጨፈጨፉን እልም ያሉ አረመኔዎች ናቸው» የሚል ምሬትና ለቅሶ ግፉአን በእንባ እየተራጩ ከነገሩት በኋላ ነው።

ብአዴን ሕዝብ እንዲህ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ከተማው ጭምር የደም እንባ እያነባ ያሰማውን የሐዘን ለቅሶና ምሬት ጆሮ ዳባ ልሰብ ብሎ የአማራን ሕዝብ ያወገዘበትን መግለጫ ያወጣው የአማራ ሕዝብ አካል ስላልሆነና አማራውን በጠላትነት ፈርጀው እየጨፈጨፉን ያሉት የተከዘ ማዶ ፋሽስቶች አገር በቀል ወኪል ስለሆነ ነው።

ለዚህም ነው ባለፈው በጻፍነው አማራው ግብር እየከፈለ የሚቀልበው ነውረኛው ብአዴን እርመ በልና ሰብአዊነት የሌላቸው ወደር የማይገኝላቸው የሕዝብ ጠላቶች ያልነው።

Share to friends and family
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

About Zsunshinetube

Each one of us must take personal responsibility to speak up, stand up and defends for each other regardless of ethnicity, religion or any other.
View all posts by Zsunshinetube →

Leave a Reply