“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር” የቴዲ አፍሮ የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር”

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር” በሚል መሪ ቃል የተሰየመውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በባህርዳር እንደሚቀርብ ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ዛሬ አስታውቋል። ሙሉ መግለጫውን እነሆ

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ”
የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር

ቅዳሜ ጥር 12 ቀን በአማራ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በሆነችው በውቧ ባሕር ዳር ከተማ ከ80 ሺሕ ሕዝብ በላይ ማስተናገድ በሚችለው በታላቁ ብሄራዊ ስታዲየም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር የሙዚቃ ዝግጅቴን እንዳቀርብ ለአማራ ክልላዊ መንግስት፣ ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችንን አቅርበን የነበረ ሲሆን ፤ ጥያቄያችንን የተመለከቱት ሁሉም አካላት ያለ አንዳች ቢሮክራሲና እንግልት በጠየቅነው ቦታና ዕለት የሙዚቃ ድግሳችንን ለቱሪስት መስህቧ ባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፣ ከመላው የአገራችን ክፍል ለሚመጡት የሙዚቃ አፍቃሪዎችና አለም አቀፍ ቱሪስቶች ማቅረብ እንድንችል የፈቀዱልን በመሆኑ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል።

እኔም ወደ ሙዚቃው አለም ከገባሁበት በተለይም የመጀመሪዬ አልበሜ ከሆነችው አቡጊዳ ጀምሮ በቅርብ እስካሳተምኩት 5ኛው አለበሜ “ኢትዮጵያ” ድረስ ከፍተኛ ፍቅር የለገሰኝን የሙዚቃ አፍቃሪ ለማስደሰት ከአቡጊዳ ባንድ ጋር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስንሆን፤ ቅዳሜ ጥር 12 ቀን ለመገናኘት ያብቃን እላለሁ።

ከሁሉ አስቀድሞ ይህ ሁሉ ይሆን ዘንድ ፈቃዱ የሆነውን ቅዱስ እግዚአብሄርን ክብር መስጋና ይድረሰው እያልኩ ፤ ለጥያቄያችን አወንታዊ መልስ በመስጠትና ጥር 12 ቀን የምናቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉልን፡
ለአማራ ክልላዊ መንግስት
ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት
በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጋችሁት ለባሕር ዳር ከተማና አካባባዋ ወጣቶች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይህ የሙዚቃ ዝግጅታችን በሌሎችም የአገራችን ከተሞች የሚቀጥል ሲሆን ጊዜው ሲፈቅድ ዝግጅታችንን የምናቀርብባቸውን ቦታዎችና ቀኑን እናሳውቃለን።

ባሕር ዳር ጥር 12 ቀን በታላቁ ብሔራዊ ስታዲዬም በሰላም ያገናኘን !

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

Spread the love
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
, ,

About Zsunshinetube

Each one of us must take personal responsibility to speak up, stand up and defends for each other regardless of ethnicity, religion or any other.
View all posts by Zsunshinetube →

1 thought on ““ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር” የቴዲ አፍሮ የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር

 1. ጥበበኛው ቴዲ አፍሮ
  ጥር 12 ቀን፥ ባህርዳር ላይ የሙዚቃ ድግስ እንደምታቀርብ የተረጋገጠ ነው! ግን የአካባቢው ህዝብ የቅዱስ ሚካኤል ንግስ ስላለበት፥ ቀኑን ታስተካክል ዘንድ፥ በአክብሮት እንጠይቃለን!! ንግስ እንዳታስተጓጉል አደራ ይሁንብህ! ህዝብ የሚወድህ ለህዝብ የማይመች ስራ ስለማትሰራ ነው! እናም በመንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ላይ፥ ዓለማዊ ሙዚቃ ነውር መሆኑን ታጣዋለህ ብየ ሳይሆን፥ ለማስታወስ ወይንም ለማሳሰብ ፈልጌ ነው! እንዳውም ያኔ’ኮ የየካው ሚካኤልን የምታጀብ መስሎኝ ነበር፥ ጥብቅ የተዋህዶ ልጅ መሆንህን አቃለሁና! ፍቅር ያሸንፋል!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *