መቼ ነው ሙላትሽ? (ትዕግስት አለምነህ)

መቼ ነው ሙላትሽ?

አንቺ ውብ ጨረቃ
‘ባንድ ጎን ፈንጥቀሽ
‘ባንዱ ተደብቀሽ

በከፊል ብርሃን በከፊል አንቺነት
በግማሽ ጨለማ በግማሽ ማንነት

በጥቁር ሰማይ ላይ ዛሬም አይሻለሁ
በድቅድቁ መሃል እከተልሻለሁ

እስቲ ተጠየቂ እባክሽ እናውራ
መቼ ነው ምትሞይ አለሜ እንዲበራ?

ትዕግስት አለምነህ

Share to friends and family
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

About Zsunshinetube

Each one of us must take personal responsibility to speak up, stand up and defends for each other regardless of ethnicity, religion or any other.
View all posts by Zsunshinetube →

Leave a Reply