የፖለቲካ እስረኞች አርብ ወይም ቅዳሜ ይፈታሉ ተባለ

ሃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ከሌሎች የክልል መሪዎች ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ አንዳንድ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ በገለጹት መሠረት እስረኞች ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ወይም ቅዳሜ ታኅሳስ 28 ቀን እንደሚፈቱ ተዘገበ::

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው የታሰሩ ወገኖች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ሲሆነ የትኞቹ ተፈተው የትኞቹ እንደሚቀሩ የተገለጸ ነገር የለም::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፈታሉ ያሏቸው እስረኞች “አንዳንድ” በሚል የተገለጸ በመሆኑ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንደማይለቀቁ ከወዲሁ እየተገለጸ ነው::

ይህን ተከትሎ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የሰጠው አስተያየት የሚከተለው ነው::

~በርካታ የፓርቲ አባላት በታሰሩበት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ብቻ እንፈታለን ከተባለ ለቀሪዎቹ ንቀት ነው!
~ የፓርቲ አባላትን ፈተቶ በአማራና ኦሮሞ ህዝብ አመፅ ሰበብ የተከሰሱትን አርሶ አደሮች አልፈታም ማለት ለ70 ሚሊዮን ህዝብ ንቀት ነው!
~እነ አህመዲን ጀበልን አለመፍታት ለሙስሊሙ ንቀት ነው!
~ የዋልድባ መነኮሳትን አለመፍታት ለክስርትያኑ ንቀትነው!
~ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን አለመፍታት ለአማራ ህዝብ ንቀት ነው!
~……… ለኢትዮጵያ ህዝብ ንቀት ነው!
~…………… ንቀት!
√ የተናቀው ህዝብ ምን እንደሚያደርግ ደግሞ ባለፉት ሁለት አመታት ታይቷል!

Share to friends and family
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

About Zsunshinetube

Each one of us must take personal responsibility to speak up, stand up and defends for each other regardless of ethnicity, religion or any other.
View all posts by Zsunshinetube →

Leave a Reply