ህወሃት ን ማመን ቀብሮ ነው – መስቀሉ አየለ

ለወያኔ ስዕለ ማርያም እቤቴ ድረስ መጥታ እንዴት እምቢኝ እላለሁ ብሎ ማመን ደካማ ጎን ነው።

ራስ ስሁለ ሚካኤል የተባለ የትግራይ ገዥ በዘመኑ የነበሩትን የሃማሴን ገዥ በመካከላቸው ስለነበረው ቁርሾ ተነጋግረው ይፈቱት ዘንድ ሽማግሌ ላከባቸው።

ሰውየው ሰምተው እንዳልሰሙ ዝም አሉ፤ ባያምኑት ነው። ለሁለተኛ ግዜ ስእለ አድህኖ አስይዞ ቄስ ቢልክባቸው ምስለ ፍቁር ወልዳ ከቤቴ ድረስ መጥታ እንዴት እንቢ እላለሁ ሲሉ ቄሱን ተከትለው ወደ ትግራይ ቢሄዱ እጅና እግራቸውን በእግረ ሙቅ አስሮ ከበረት ወርውሯቸዋል።

ለወያኔ ስእለ ማርያም እቤቴ ድረስ መጥታ እንዴት እምቢኝ እላለሁ ብሎ ማመን ደካማ ጎን ነው። ትናንት የጎንደሩን አመጽ ተከትሎ ለተጋድሎ የወጡትን አርበኞች ታቦት ጭምር እያስያዘ መሳሪያ ካስፈታ ቦሃላ ከተኙበት ከሌሊት እያነቀ ወስዶ የፈጃቸውን ወገኖቻችንን ቤት ይቁጠረው

ከዛን ግዜ ጀምሮ የትግሬዎች ተረት “ዶሮን በባቄላ ሃማሴንን በመሃላ” የምትል ሆና የምትኖር ቢሆንም ቅሉ የዚህች ተረት ትርጉም ለሻቢያ ሰዎች ሳይቀር ስጋና ደም ገዝታ በአካል ገዝፋ የታየቻቸው ባድመን ምክንያት አድርጎ ከጀርባ በወጋቸው ግዜ ነው።

ፈረንጆቹ የጠላትን ክፉ ሲገልጡት “ባክ ስታበር” ይሉታል። ዛሬ ወያኔ ከኳታር እስከ ላቲን አሜሪካዋ ብራዚል፤ ከሃይሌ ገብረ ስላሴ እስከ አውሮፓ ህብረት ሰባ ሁለት ግዜ ያህል ወደ ሻቢያ አስታራቂ ሽምግሌ ቢልክም የሽቢያ መልስ ጆሮ ዳባ ልበስ የሆነው ከዚህች ዘመን የማይሽራት ጠባሳ ታሪክ ተነስቶ ነው። ሁለት ግዜ ስ ህተት ብሎ ነገር የለም።

የቅንጅት መሪዎች ከዚያ ሁሉ አገር አቀፍ ንቅናቄና የፖለቲካና የሞራል የበላይነት በኋላ እግር ተወርች ታስረው ዘብጥያ መውረዳቸው ብቻ ሳይሆን ስንት የእንጨት ለቃሚ ደሃ ልጆችን አናት ያበደ ዝሆን በሚገደልበት እስታይፐር አናታቸውን እንደ ፓፓየ ላፈረጣቸው አጋዚ “ሃላፊነቱ የኛ ነው” ብለው፤ “አይለመደንም” ብለው፤ መቀለጃ ሆነው መውጣታቸው ብቻ እንዲሁም እነርሱ በሰሩት ጥፋት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ምን ያህል አመት ወደ ኋላ እንደጎተቱት ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት ያማል።

ወያኔ ዛሬ ድረስ እድሜ አግኝቶ የአገራችን ፖለቲካ አስፈሪ ወደ ሆነ የጽንፈኝነት ጥግ እንዲደርስ የቅንጅት ሰዎች ሰርተው ያለፉት ታሪካዊ ስህተት የራሱን አሉታዊ ሚና መጫዎቱን መካድ አይቻልም።

በእርግጥም ይኽ ወቅት የአገራችን ምሁራን እውቀት በወረቀት ላይ የተንጠለጠለ እንጅ ነባራዊ ከሆነው የአገራችንን ችግር ከመፍታት አንጻር ብዙ እንደሚቀረው ያሳየ እንደነበር ምስኪኑ ህዝብ በወቅቱ ሲሰጥ ከነበረው ማስጠንቀቂያ መረዳት ይቻላል።

ዛሬ የገዱና የለማ መገርሳ መንገድ መስቀለኛ ነጥብ ላይ መቆሙ ሌላው ዙር የታሪክ ሂደት ነው። እንደ ወያኔ ያለ ጭንቅላታቸው ገና ከናታቸው ማህጸን ውስጥ ሳሉ በጨነገፈባቸው ድኩማን የሚዘወር ድርጅት አለም ላይ የተፈጠሩት ኩነቶች አሲረውለትና በሻቢያ ታንክ ታዝሎ አዲስ አበባ መግባቱን እንደራሱ የድል ውጤት በመቁጠር እሾክና ግርምቢጥ ካልሆነ ሌላ ነገር ከማይደማው እርጉም ምድር መምጣቱንም ሆነ በቁጥር ደረጃ እዚህ ግባ የማይባል አናሳ ህዝብ መወከሉን እረስቶት በኢትዮጵያዊነት ካባ ከመድመቅ ይልቅ አገሪቱን በምርኮ እንደተያዘች የንጉስ ሚስት ክብሯን በመገሰስ ላይ ሲዘምት እንዳልኖረ ይኽ ቅጥ ያጣው ብልግናው፣ ውሸቱ፣ እብሪቱ፣ ዘረፋው፣ ድንቁርናው ሁሉ ግዜውን ጠብቆ ግዜ ከፈጠረው እውነታ ( ሪያሊቲ) ጋር ተፋጠጠ።

የርሱን ቋንቋ እየተናገሩ ነገር ግን ባርነት በቃን ብለው የጉሮሮ አጥት መሆን የቻሉ ሰዎች ከመሃሉ ጎልምሰው ሲወጡ የሚሸሸግበት ጥግ ማጣቱን፣ የሚቀጥፍበት አማርኛ መንጠፉን ይኽ ገዜ አስይቶናል።

 

መሳይ መኮንን ዘብሔረ ኢሳት በዝርዝር እንደሄደበት የትግራዩ ገዝ ጉጅሌ ዕከመከላከያ እስከ ደህንነት፣ ቁልፍ ከሆኑ የሚንስትር ቦታዎች እስከ ወልቃትይ ጠገዴ ለድርድር የማላቀርበው ነገር የለም።

ብቻ ይኽን ህዝባዊ ማእበል ወደ ሰገባህ ተመለስ በሉልን እንጅ ይኽ አብዮት አባይ ጸሃየንና አዜብ ጎላን በልቶ የሚቆምልን ከሆነ እነርሱንም ጭዳ አድርጎ ለማቀረብ ችግር የለብንምዕ ሲል በእንባ ጭምር ልመና ማቅረቡን ተረድተናል።

ቀጣዩ የአገሪቱ አቅጣጫ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ይወሰናል።

 1. ህወሃት ከላይ በምሳሌ እንዳስቀመጥኩት በባህሪው የማይታመን ለመሆኑ ከዘርማንዘሮቹ ታሪክና እስካሁን የተጓዘበትን መንገድ እንደምሳሌ ጠቅሻለሁ። ስለዚህ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብም ይሁን እሳቱን ከፊት የተጋፈጠው የገዱ ለማ ጥምረት በምን ያህል መተማመኛ ይቀበለዋል፧፣ አልቀበልም ካለስ ቀጣዩ መውጫ መንገድ ወይንም ኤክሲት ስትራቴጅ ምንድን ነው፧
 2. የገዱ ለማ አካሄድ እንደ ቅንጅት ሰዎች ሁሉ አሁን የያዙት አካሄድ ዕህገ መንግስታዊ መብታችን ስለሆነ ነውዕ ከሚል ጭፍን እምነት ተነስተው ነው ወይንስ ህዝባዊ ማእበሉ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ በደንብ ተገንዝበው፣ ወያኔስ ልመናውም ሆነ ማስፈራራቱም አልሳካለት ሲል በመጨረሻ ለሚመዘው ሰይፍ ምን ያህል ተዘጋጅተዋል የሚሉት ቁልፍ ጥያቄዎች ናቸው።

እንደ ማሳሰቢያ
ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሚወጡት ፍንጮች ከሆነ የአሜሪካ መንግስት አሁን የደረሰበት የድምዳሜ ደረጃ ወያኔ ይበልጥ እድሜ እያገኘ በሄደ ቁጥር አገሪቱ ይበልጥ ወደ አደገኛ አቅጣጫ እየተገፋች ስለሆነ የሽግግር ሂደቱ አካል ሊሆን አይገባውም።

የእንግሊዝ መንግስት ደግሞ በተጻራሪው ወያኔን ራሱን ሪፎርም አድርጎ ማስቀጠሉ የተሻለ ነው የሚል አቋም በመያዙ የገዱ ለማ ጥምረት የውጭ መንግስታትን አካሄድ በሰከነ መንፈስ እንዲመረምር ግድ ይለዋል።

Share to friends and family
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  

Leave a Reply