የትግራይ የበላይነት ስንል…በስዩም ተሾመ

የአንድ ቡድን የበላይነት አለ!

የአንድ ቡድን የበላይነት ማለት በአስተዳደራዊ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ የስልጣን እርከኖችን መቆጣጠር አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ የፖለቲካ ሳይንስ የሚለው የአንድ ቡድን የበላይነት የሚረጋገጠው፤

 1. “አስተዳደራዊ ስርዓቱ የሚተዳደርበትን የህግ ማዕቀፍ በራስ ፍላጎትና ግንዛቤ መሠረት በማፅደቅና ተግባራዊ በማድረግ” እና
 2. “ይህ አስተዳደራዊ ስርዓት በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይት እንዲያገኝ የቡድኑ ደጋፊ ለሆኑ የፖለቲካ ልሂቃን አድሏዊ ድጋፍና ማበረታቻ በማድረግ ነው”፡፡

በዚህ መሠረት፣ “ሀገሪቱ የምትተዳደርበት ህገ መንግስት በዋናነት በህወሓት ፍላጎት እና የፖለቲካ አቋምና አመለካከት መሠረት የረቀቀ፥ የፀደቀና ተግባራዊ እየተደረገ ያለ ነው!” ብለን ስንል “ለትግራይ ህዝብ ጥላቻ ስላለህ ነው” ይሉሃል፡፡

“እነ እስክንድር ነጋ በእስር እየማቀቁ፣ እነ አብይ ተ/ማሪያም፥ መስፍን ነጋሽ፣ ታምራት ነገራ…ወዘተ በስደት እየኖሩ እንደ ፍፁም ብርሃኔ፥ ዘርዓይ ሃ/ማሪያም እና ሰናይት መብራቱ እንደ አሻቸው በህወሓት እየተከፈላቸው በነፃነት መዘላበዳቸው የህወሓት የበላይነት ማረጋገጫ ነው” ብለን ስንናገር “ለትግራይ ህዝብ ጥላቻ ስላለህ ነው” ይሉሃል፡፡

አጎቴ ዳንጎቴ’ማ በአቶ ጌታቸው ረዳ ዘመን “በአማካሪነት” ስም በየወሩ ከሚከፈለው 15,000 ብር በተጨማሪ የሚፅፍበት ኮምፒውተርና CDMAን ጨምሮ የመንግስት ኮሚዮኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት መሆናቸውን ስሰማ፣ “ጌቾ” የፅ/ቤቱ ሃላፊ ሆኖ የተመረጠ ሰሞን ጭራውን ቆልፎ ሲጨፍር የነበረው ትዝ ብሎኝ “ክት-ክት” ብዬ ሳቅኩ፡፡

እኔ “ክትክት” ብዬ ስስቅ በከፊል ለፈጠሪ እናንተን “እንክትክት” ያደርግልኝ ዘንድ እየፀለይኩ ነው፡፡ ፈጣሪ ቢሰማኝ (አይሰማኝም እንጂ) ፀሎቴ ከሰይጣን ሞት ይልቅ ከህወሓት ለህወሓት ውድቀት ነው፡፡ ምክንያቱም፣

 1. ምንም ዓይነት ሳይንስና ምክንያት ቢነግሯቸው ፈፅሞ የማይገባቸው የደናቁርት ስብስብ በመሆናቸው፣
 2. በትግራይ ህዝብ ስም ኢትዮጲያን መዝረፋቸው ሳያንስ “የትግራይ ህዝብን ትጠላለህ!” የሚለው ድርቅናቸው፡፡

በትግራይ ህዝብ ስም ሀገር እያፈረሱ፥ እያቆሰሉና እየገደሉ የጥቅም ሱሳቸውንና የበታችነት ስሜት ቁርጥማታቸው ከሚያስታምሙ ድኩማኖች በስተቀር የትግራይ ህዝብ ሆነ የኢትዮጲያ ህዝብ ጠላት የለም፡፡ እነሱ “የትግራይ ህዝብን ትጠላላችሁ!” ሲሏችሁ መልሱ “አዎ” ነው፡፡ ምክንያቱም እውነቱ እነሱ ካሉት ተቃራኒ ነውና!!

Share to friends and family
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  

Leave a Reply