ስዋንሲ ሲቲ ፓል ኬለመንትን ካሰናበተ በኋላ በጊዜያዊነት ክለቡን የሚያሰለጥነውን ሰው ይፋ አደረገ

ስዋንሲ ሲቲ ፓል ኬለመንትን ካሰናበተ በኋላ በጊዜያዊነት ክለቡን የሚያሰለጥነውን ሰው ይፋ አደረገ።

Mikiyas B Wordofa

ፖል ኬለመንትን ለመተካት አማራጮችን እየተመለከተ የሚገኘው ስዋንሲ ሲቲ በመጪው ቅዳሜ በሜዳው በሚያደርገው ጨዋታ ሊኦን ብሪቴን ቡድኑን በተጠባባቂ አሰልጣኝነት እየመሩ ወደሜዳ እንደሚገቡ አስታውቋል። ትናንት ምሽት አሰልጣኝ ክሌመንትን ያሰናበተው የፕሪምየር ሊጉ ክለብ የያዝነው ሳምንት ከመጠናቀቁ በፊት ቋሚ አሰልጣኝ ለመቅጠር ያቀደ ቢሆንም የረጅም ጊዜ የቡድኑ አማካኝ ሆኖ ያገለገለው እና ባሳለፍነው ወር በክለቡ የአሰልጣኝነት ስራ የጀመረው ቢሪተንን ቢያንስ አንድ ጨዋታ ላይ በጊዜያዊነት ቡድኑን እንዲይዝለት መፈለጉን ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። ስዋንሲ በመግለጫው ባለፉት 15 አመታት ክለቡን ያገለገለውና እና የተጫዋች አሰልጣኝነት ተደራራቢ ሀላፊነትን በሊበሪቲው ክለብ ያገኘውን ብሪተን በረዳትነት እንዲያግዙ የክለቡ ከ 23 አመት በታች አሰልጣኝ የሆኑትን ጋሪ ሪቻርድስ እና ካሜሮን ቴሻክ በምክትልነት መሾሙን አያይዞ ገልጿል።

Share to friends and family
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

Leave a Reply