መረጃ – ሃብታሙ አያሌው 

ጥብቅ መረጃ

መረጃ – ህወሓት ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ የሚያገኘው የመጨረሻ ውጤት ለጥቂት ጊዜ በግንባሩ ውስጥ በተስማምተናል ሂሳብ እንደ ጥልቅ ተሃድሶው እወጃ ጊዜ መግዛት ካልሆነ በቀር ሌላ ውጤት ሊገኝ እንደማይችል ቁርጣቸውን አውቀዋል።

 

ይሄም ቢሆን ከስብሰባው መጠናቀቅ በፊት ኃይለማርያም ተፅፎ የተሰጠውን መግለጫ እንዲያነብ፤ መከላከያ ሰራዊት ኦሮሚያና አማራ ክልልን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ትዕዛዝ በመስጠት በስብሰባው ህወሓትን ወክሎ ማስፈራርያውን የሰነዘረው ጌታቸው አሰፋ (የመረጃና ደህንነት ኃላፊው ) “ግምባሩ መስማማት ካልቻለ ፌደራል ስርዓቱ አይፈርስም መከላከያ ህገ መንግስቱን ያስከብራል፤ አዝማሚያችሁ ግልፅ ስለሆነ (ኦህዴድና ብአዴንን ) መሆኑ ነው፤ ለአደጋ ያጋለጣችሁትን የትግራይ ህዝብ የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፤ እስካልተስማማችሁ ኢህአዴግ ይፈርሳል ስርዓቱን መከላከያው ይጠብቃል ” ኮምጨጭ ያለ የእብሪት ንግግር ማድረጉ ታውቋል።

ይህንን ተከትሎ ጫናው የወለደው መግለጫ ስብሰባው ሳያልቅ ቢወጣም፤ ኃይለማርያም መግለጫ ቢሰጥም ጥቂት ጊዜ መግዛት ቢቻል እንኳ ፈፅሞ ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ እንደማይችል ግልፅ በመሆኑ ትላንት እረቡ ማምሻውን ከወልዲያ ዩኒቨርስቲ የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ አስወጥተው ወደ መቀሌ ማጓጓዛቸውን ከስፍራው መረጃ ተገኝቷል።

በመከላከያ ሰራዊት ታጅበው የወጡት ተማሪዎች በግልፅ “ተመልሰን እንመጣለን በቦንብ እናጋየዋለን እንጂ አትማሩበትም” በማለት እየዛቱ በመሄዳቸው የመከላከያ አዛዦች ለተማሪዎቹ ዛቻ ድጋፍ ያሳዩ መሆኑ በቀሪዎቹ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረ። መረጃውን ያደረሱኝ አያይዘው ጠቁመዋል።

Share to friends and family
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

Leave a Reply